የኦሮሚያ የጸጥታ ሃይሎች በአካራሪ የፋኖ ሃይሎች ተገደሉ ።

Facebook
Twitter
LinkedIn
Print

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ጡጡጢ ቀበሌ ልዩ ሰሙ ቆርኬ ተብሎ በሚታወቅ ሰፍራ ላይ የአማራ ሃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት ከ27 በላይ የኦሮሚያ የጸጥታ የሃይሎች በ 29/03/2022 መሞታቸው ተነግሯል ።

ጥቃቱን የሰነዘሩት አክራሪ የአማራ ሃይሎች በተደጋጋሚ በአከባቢው የኦሮሞ ህዝብ ላይ ወረራን ፈጽመዋል።

ከተቆጣጠሯቸው አከባቢዎች መካካል “ቋርኬ” የተባለን አከባቢ ስም በመቀየር  “በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራጎዳና” የሚል ስያሜ መስጠታቸውም ተነግሯል ።

ከአከባቢው ኦሮሚያ 11 ያነጋገርናቸው ምንጮች እነኚህ ሃይሎች የፌደራል መንግስት ድጋፍ አላቸው ብለው እንደሚየምኑ ነግረውናል።

ባለፈው መክሰኞ (29/03/2022) አንድ መቶ የሚጠጉ ሚሊሻዎች ከቦሰት ወረዳ  ወደ መታሃራ በመመለስ ላይ እያሉ መኪናቸው ላይ በተከፈተ ተኩስ መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አረጋግጧል ።

የሚሊሻ አዛዥን ጨምሮ  ከ27 በላይ የጸጥታ ሃይሎች በአማራ ክልል አክራሪ ሃይሎች በጅምላ መገደላቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ ።

የአማራ ክልል መንግስት ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሚዲያዎች  ጥቃቱ የደረሰበትን ቦታ ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ብለው መዘገባቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

Facebook
Twitter
LinkedIn
Print
Scroll to Top
Days :
Hours :
Minutes :
Seconds

Happy New year 2024

warra Baranaa kan bara hedduu