እንደምታወቀው ዓለማችን በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ከተወረረችና የብዙ ንጹሃን ነፍስ መርገፍ ከጀመረ ጥቂት አመታቶች እየተቆጠሩ ነው።
ዛሬ ላይ የነጻ ኽትባቶች በዓለማችን ላይ በመሰራጨት ላይ ብገኙም ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም አልቻለም። ይሁን እንጂ ሰዎች ኽትባቱን በመውሰድ እራሳቸውን ለመከላከል ችለዋል። በኣሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያንም ይህንን አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች።
ይህ የነጻ ኽትባት የሚሰጥበት ቦታ እዛው የ ቤተክርስትያኒቷ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ሲሆን፣ አድራሻው 2601 Minnehaha Avenue Minneapolis, MN,55401 ነው። ለበለጠ መረጃ ደግሞ በ 612-251-1961 በመደወል ይጠይቁ።