አለማችን አሁንም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እውቂያኖስ መናወጧ አላበቃም። ሞት፣የህመም አንግልት እና ወዘተ፣ አሁንም የሰዎችን ጓዳ መዳሰሱ አልቆመም። ዓለም ይህን ቀጣፊ ቫይረስ ተረባርባ ለማጥፋት ደፋ ቀና ብትልም እንዳሰበችው የንጹሃንን ሞት ሙሉ በሙሉ ማስቆም አልቻለችም። ለዚህ ነው እስካሁንም ሰዎች እየተጠቁ የሚገኙት። ቫይረሱ እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም ድረስ መሰራጨቱን አላቆመም።

ሚኒሶታ ውስጥ ክትባት በነጻ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?
አዎን አሜሪካ ልክ እንደ ስሟ አሜሪካ። ለዜጎቿ ጤንነት ስትል የማታረገው ነገር አይኖርም። ለዚህም ስትል በየ እስቴቱ የክትባት መዓከላቶችን አቋቁማ ለዜጎቿ የነጻ ክትባቶችን እየሰጠች ትገኛለች። ከ አሜሪካ ግዛቶች አንዷ የሆነችው ሚኒሶታም ይህን የነጻ አገልግሎት ለዜጎ በየ ጤና መዓከላቶች፣ቤተ እምነቶች፣መዝናኛ መዓከላቶች እና ትላልቅ የትምህርት ኢንስቲትዩት ውስጥ ሁኔታዎችን አመቻችታ አገልግሎት በ መስጠት ላይ ትገኛለች። እስካሁን የመከተብ እድሉን አግኝታችሁ ያልተከተባችሁ ሁሉ በዚህ እድል እንድትጠቀሙ መልዕክታችንን ማስተላለፍ እንወዳለን። በ ነጻ ክትባቱን መውሰድ የምትፈልጉ ሠዎች ከዚህ በታች ምስሉ ላይ በምታገኙት መረጃ መሰረት ክትባቶትን ሄደው መውሰድ ይችላሉ።